top of page
Search

COVID-19 (በፊት "ኖቬል ኮሮናቫይረስ” ተብሎ የሚታወቀዉ) የህዝብ ጤና ምክረ ሀሳቦች |

COVID-19 ምንድነዉ?

COVID-19 (በፊት "ኖቬል ኮሮናቫይረስ” ተብሎ የሚታወቀዉ) ከሰዉ ወደ ሰዉ እየተሰራጨ ያለ አዲስ ቫይረስ ነዉ። ምንጩ ከቻይና ሆኖ በአሁኑ ሰዓት አሜሪካና ብዙ ሌሎች አገሮች ይገኛል።

እንዴት ነዉ ኖቬል ኮሮናቫይረስ (COVID-19) የሚሰራጨው?


የጤና ባለሙያዎች ስለስርጭቱ አሁንም ተጨማሪ እየተማሩ ነው። በአሁኑ ሰዓት ይሰራጫል ተብሎ የሚታሰበዉ፡ በበሽታዉ የተየዘ ሰዉ ስያስነጥስና ስያስል በትንፋሽ ጠብታዎች ዉስጥ ቅርብ ለቅርብ በሆኑ ሰዎች መካካል (በ6 ጫማ ርቀት ዉስጥ) ቫይረሱ ያለበት ነገር ከነኩ በኋላ አፍ አፍንጫ ወይንም ዐይን በመንካት

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጠባቸው ሰዎች ለቫይረሱ ከተጋለጡ በኋላ ቢያንስ በ2 ቀናት ውስጥ ወይም ቢበዛ እስከ 14 ቀናት ድረስ ምልክቶች ይታዩባቸዋል።


ትኩሳት ፥ ሳል ፥ ለመተንፈስ መቸገር


  1. ለከፋ የ COVID-19 በሽታ በከፍተኛ የተጋላጭነት ስጋት ላለባቸዉ ሰዎች ምክር የህዝብ ጤና ለከፋ ህመም ተጋላጭነት ስጋት ላለበቸው ሰዎች ቤት እንዲቀመጡና ብዙ ሰዎች ካሉበት ስፍራ በተቻለ መጠን እንዲርቁ ይመክራል። የከፋ ህመም ተጋላጭነት ስጋት ያለባቸው ሰዎች የሚጨምረዉ፡ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሌላ ቀደም ያለ የጤና ችግር ያለባቸው፤ የልብ ህመም፣ ሳምባ በሽታ ወይንም ስኳር ያለባቸውን ጨምሮ በሽታ የመከላከል አቅማቸዉ ደካማ የሆኑ እርጉዝ የሆኑማንኛዉም የጤናቸው ሁኔታ ለከፋ COVID-19 ህመም ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸዉ ጥያቄ ካላቸው ከሃኪሞቹ ጋር መማከር አለባቸው::

  2. ለትምህርት ቤቶች ምክር ስለ COVID-19 ክስተቶች ያለዉ መረጃ ልጆችና ወጣቶች በዚህ ቫይረስ ከሚደርስ ከባድ ህመም በከፍተኛ ተጋላጭ እንዳልሆኑ ያሳያል። ምክረ ሃሳብ ስንሰጥ የመዝጋት ጠቀሜታዎችንና አሉታዊ መዘዞችን ከግምት እናስገባለን። የህዝብ ጤና በአሁኑ ሰዓት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ አይመክርም። የተረጋገጠ የCOVID-19 ክስተት ካለ፣ የህዝብ ጤና ከትምህርት ቤቱ ጋር በመስራት ምርጥ እርምጃዎችን ትምህርት ቤት መዝጋትን ጭምር ይወስናል። ለትምህርት ቤቶች እንዴት ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ክፍት ሆኖ መቆየት እንደሚቻል መረጃ እንሰጣለን።አንዳንድ ልጆችና ሰራተኞች የጤና ሁኔታቸው ሰዉነትን የመከላከል ሃይላቸው ደካማ ስለሆነ በከፍተኛ ተጋላጭ የሚያረጋቸው የጤና እክል አላቸው። ቀደም ያለ የጤና እክል ያለባቸዉን ልጆች የሚንከባከቡ ሰዎች ልጆቹ ቤት ይቆዩ አይቆዩ ለሚለዉ ከሃኪሞቻቸዉ ጋ መማከር አለባቸዉ።

  3. ለስራ ቦታዎችና ድርጅቶች ምከር

ከቤት ሆኖ የመስራት አማራጮችን ለሰራተኞች ማብዛት ሰራተኞች ከታመሙ ቤት እንዲሆኑ መገፋፋት ለታመሙ ወይንም ተጋላጭነታቸዉ ከፍ ያለ ስለሆነ ቤት እንዲሆኑ ለተመከሩ የህመም ጊዜ እረፍት ፈቃዳቻዉን ከፍ አድርጎ ማመቻቸት ብዙ ሰዎች ባንድ ጊዜ መምጣትን ለመቀነስ የስራ መግቢያና መዉጫ ሰዓቶችን ማለያየት

ቀጣሪዎች ሰራተኞቻቸዉ ከብዙ ሰዎች ጋር መገናኘት ሊቀንሱ በሚችሉባቸዉ መንገዶች እንዲሰሩ ለማመቻቸት እርምጃዎች መዉሰድ አለባቸው። ቀጣሪዎች ማድረግ ያለባቸዉ፣


  1. ለኩነት ና የማህበረሰብ ስብሰባዎች ከግምት የሚገቡ ነገሮች የታመመ ሰዉ እንዳይሳተፍ መገፋፋት ለ COVID-19 በከፍተኛ ተጋላጭ የሆኑትን እንዳይሳተፉ ማበረታታት ለሰዎች ብዙ ክፍተት ለመስጠት መንገድ መፈለግ በተቻለ መጠን ቅርብ ለቅርብ እንዳይሆኑ ተሳታፊዎችን እንደ ቶሎ ቶሎ እጅ መታጠብ ያሉትን መልካም ልማዶችን እንዲቀጥሉበት ማበረታታት በየጊዜዉ ነገሮችን ላያቸዉን ማጽዳጥ። መደበኛ ማጽጃዎች በCOVID-19 ላይ ዉጤታማ ናቸው። በዚህ ወሳኝ የድንገተኛ ወቅት ከተቻለ ብዛት ያለቸዉን ሰዎች አንድ ላይ ማምጣትን ማስወገድ፣ ኩነቶችንና ስብስባዎችን ማስተላለፍ። ሰዎች አንድ ላይ ማምጣትን ማስወገድ የማይችሉ ከሆነ፤

  2. ለሁሉም ሰዉ ምክር ቤት ይቆዩ በተጨማሪም ሲታመሙ ህዝብ ወዳለበት እንዳይወጡ። አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ህክምና አካባቢ መሆንን ማስወገድ። ሆኖም ከታመሙ ወደ ዶክተርዎ ቢሮ ከመሄድዎ በፊት ይደዉሉ። ባይታመሙም እንኳን በተቻለ መጠን ሆስፒታሎችን፣ የረጅም ግዜ መንከባከቢያ ቦታዎችን ወይንም ነርሲንግ ቤቶችን መጎብኘትን ያስወግዱ። ከነዚህ ቦታዎች አንዱ ጋ መሄድ ካለብዎት፣ ከዚያ የሚቆዩበትን ግዜ ይገድቡ በተጨማሪም 6 ጫማ ከታማሚዎች ይራቁ። አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ድንገተኛ ክፍሎች እንዳይሄዱ። የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቶች ቅድምያ በጣም ለተጎዱት ነዉ ማገለገል ያለባቸዉ። ሳል፣ ትኩሳት ወይንም ሌላ ምልክት ካለብዎ መጀመሪያ መደበኛ ዶክተርዎ ይደዉሉ። እጅዎን በሳሙናና ዉሃ በየጊዜዉ መታጠብ፣ በሶፍት ወይንም ክንድዎ ላይ ማሰል፣ ና ዐይኖን፣አፍንጫ፣ ወይንም አፎን መንካት ማስወገድን ጭምር ያሉትን ምርጥ የግል ንጽህና ልማዶችን ያድርጉ። በተለይ ለኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ተጋላጭነት ስጋት ያለብዎት ከሆኑ ከታመሙ ሰዎች ይራቁ። በየጊዜው የሚነኩ እቃዎችንና ላያቸዉን ያጽዱ (እንደ በር እጀታዎችና መብራት ማብሪያ/ማጥፊያዎች)። መደበኛ የቤት ማጽጃዎች ዉጤታማ ናቸዉ። ብዙ እረፍት ያግኙ፤ ብዙ ፈሳሽ መጠጣት፤ ጤናማ ምግቦችን መብላት ና ጫናዎትን መቆጣጠር የሰዉነትዎን በሽታ የመከላከል ችሎታን ጠንካራ እንደሆነ ለመጠበቅ። ከርስዎ በተለይ ደግሞ ለCOVID-19 በከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑት ስጋት ለመቀነስ፤

  3. የ COVID-19 ምልክቶች ወይንም ጥያቄዎች ካለዎት፣ መደወል የሚችሉት፤ የኪንግ ካዉንቲ የኖቬል ኮሮናቫይረስ ጥሪ ማእከል 206-477-3977። ይህ የአገልግሎት መስመር ከጧት 8 ስዓት እስከ ምሽት 7 ሰዓት በየእለቱ ክፍት ነዉ። የዋሽንግተን ስቴት የኖቬል ኮሮናቫይረስ ጥሪ ማእከል 1-800-525-0127 ና #ን ይጫኑ። ይህ የአገልግሎት መስመር ከጧት 6 ስዓት እስካ ሌሊት 10 ሰዓት በየእለቱ ክፍት ነዉ።ኦፕሬተሮቹ ከሶስተኛ ወገን አስተርጓሚ ጋር ማገናኘት ይችላሉ። የየትኛው ቋንቋ አስተርጓሚ እንደሚፈልጉ በእንግሊዘኛ መንገር መቻል አለብዎት። ለረጅም ጊዜ መስመር ላይ ልጠብቁ ይችላሉ።

እርስበርስ ለመረዳዳት ዝግጁ ሁኑ። ጠንካራ የመተሳሰብ ስሜት ከዚህ ከባድ ወቅት እንድናልፍ ይረዳናል።






በኪንግ ካውንቲ የተጻፈ

250 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page